በአዲስአበባ የመጀመርያው የ"ስፖርት ፌስት" ዝግጅት ተከፈተ

 ዜና/ስፖርት 


      photo : ሰላማዊት ላቀውና ዳዊት ትርፉ ስፓርት ፌስት ሲከፍቱ [ፎቶ ሲሳይ ጉዛይ]



ሦስት ትውልድ የሚያገናኘው ስፖርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል ትናንት 'ለት ተከፍቷል


የአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ እና በርኖስ ማስታወቂያና ኢንተርቴይመንት በጋራ ያዘጋጁት የስፖርት ፌስቲቫል። ዝግጅቱን አጠናቆ መከፈቱ ሰምተናል።


ዝግጅቱ የካቲት 8 እስከ  10 በኤግዚቪሽን ማዕከል በድምቀት ተከፍቶ ይቆያል።


ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነው ይኸው ፌስቲቫል "ስፖርት ፌስት" ይሰኛል።



 ከተመሰረት ስድስት ዓመት ያስቆጠረው በርኖስ ማስታወቂያ ድርጅት በአይነት እና በይዘት ልዩ የሆነውን ፌስቲቫል ለማዘጋጀት እና ሶስት ትውልዶችን ለማገናኘት ሰፊ ዝግጅት  ማድረጉን ታውቋል።


ስለዝግጅቱ  የበርኖስ ማስታወቂያ ድርጅት ስራ አስኪያጅ እና ባለቤት ብሩክታዊት ላቀው ከዚህ ቀደም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መዘገባችን ይታወሳል ። 


በፌስቲቫሉ 36 ፌዳሬሽኖች እና 16 ክለቦች የአዲስአበባ ክለቦች ይሳተፉበታል ተብሏል ።



በተጨማሪም  የተለያዮ በስፖርቱ ዙሪያ የሚሰሩ  ጂምናዝየም፣ የስፖርት ልብስ የሚሸጡ እንዲሁም ሌሎች የሚሳተፉ ሲሆን የተለያዮ አንጋፋ ክለቦችም  ለራሳቸውን  ያስተዋውቃሉ ተብሏል ።


ፌስቲቫሉን  150ሺ በላይ ጎብኚዎች ይጎበኙታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።


የስፖርት አፍቃሪዎች በቦታው ተገኝተው እንዲታደሙ ተጋብዛቹኋል ።



(ንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ )