ኦቪድ ሪልእስቴት ለአንድ ቀን ባዘጋጀው ልዩ የቤቶች ሽያጭ በሙሉ መሸጣቸውን ተናገረ

ቢዝነስ /ዜና




 ኦቪድ ሪልእስቴት  ለአንድ ቀን ብቻ የሚቆይ ልዩ የቤቶች ሽያጭ በታላቅ ቅናሽ (40 %)  አብዛኞቹ ቤቶች ተሸጠው መጠናቀቃቸው አስታውቋል ፡፡


 እነዚህ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች በ4 ምድብና ሳይቶች መካተታቸውን ተናግሯል ፡፡


በትላንትናው ዕለት ለህዝብ የቀረበው አንደኛው ፕሮጀክት ጫካ መኖሪያ ቤት ነው።


ሁለተኛው ሐረር ሆራይዘን ፕሮጀክት ሲሆን፤ ባለ 2 እና 3 መኝታ ቤት ዘመናዊ አፓርትመንቶችን የያዘ ነው ተብሏል ፡፡ 


ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ 8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡


ሦስተኛው ኪንግስ ታወር ሲሆን፤ ባለ1፣ ባለ2፣ ባለ3፣ እና ባለ4 መኝታ አፓርትመንቶችን ይዟል፡፡ 


 ኪንግስ ታወር ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ያካተቱ 1740 ሰፋፊ መኖሪያዎችን ያካተተ መሆኑ ታውቋል፡፡


አራተኛው አፍሪካን ሃይትስ ነው፡፡


ፕሮጀክቱ ባለ1፣ ባለ2፣ ባለ3፣ እና ባለ4 መኝታ አፓርትመንቶችን ጨምሮ 324 ቤቶችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡


ኦቪድ ግሩፕ በሥሩ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶችን ያቀፈ የኮርፖሬት ሆልዲንግ ነው፡፡


(ንጋት ፕሬስ )