ዜና
የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ላለፉት 20 አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን ከመንግሥት የተረከበውን መሬት የኮንፈረንስ አዳራሽ ማስገንባቱ ተናግሯል።
ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተው በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1996 ሲሆን እስካሁን ድረስ ያለ ኮንግረስ አዳራሽ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበርና አሁን ላይ ከመንግሥት የተመራውን ቦታ ሙሉ ለሙሉ አስገንብቶ ሊያስመርቅ መሆኑን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን መሪ ፓስተር ታሪኩ ቴዎድሮስ በመግለጫው ላይ እንደገለፁት ከመጋቢት 1 እስከ 7 ክፍት ሆኖ ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍት በማድረግ እንደሚጀመር ተናግረዋል።
የኮንፈረንስ አዳራሹ ጎተራ ማሳለጫ አከባቢ የሚገኝ ሲሆን አዳራሹ ዘመን አፈራሽ የግንባታ ስርአት የተገነባ መሆኑን ፓስተር ታሪኩ ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
በ20ኛ አመት ክብረ በዓሏ በማስመልከት አዲሱን የኮንፈረስ አዳራሽ ልታሥመርቅ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ገልፀው ቤተክርስትያኗ ከሚመለከተው ሁሉ ለተደረገላት ትብብር አመስግነዋል።
የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ላለፋት አመታት ወንጌል የመስበክ እና የማስተማር ተልዕኮ አንግባ የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች የቆየች መሆኗን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተነስቷል።
ፓስተሩ አያይዘው ቤተክርስቲያኒቱ ቀድሞ በተከራየችበት በጎተራ የእህል ንግድ ድርጅት ቅፅር ግቢ ውስጥ ላለፉት 18 አመታት የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች መቆየቱን አንስተው፣ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ባዘጋጀላት ስፍራ የራሷን የማምለኪያ አዳራሽ ገንብታ በቀጣዩ የእግዚአብሔር መንግስት ወንጌል በሐይል ለመስበክ ዝግጅቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።
ስለሆኑም የ 20ኛ አመት የምስጋና ኮንፈረንስና የአዳራሸ ምረቃ ፕሮግራም ከመጋቢት 1-7 ታላላቅ አገልጋዮችና የቤተክርስቲያን መሪዎችና አባቶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል።
በምስጋና መረኃግብሩም ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶን ጨምሮ በርካታ መዘመራንና ፓስተሮች ሳምንቱን አገልግሎት ይሰጡበታል መባሉን ሰምተናል።
ቤተክርስቲያኒቱ ትውልድ በመቅረፅ ረገድ የበኩሏን እያደረገች መሆኗንና ይህንን ድርጊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በበርቱ እንደምትሰራ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፍቃድ ማግኘቷን የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን መሪ ፓስተር ታሪኩ ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
አማኑኤል ክንደያ