ዜና/ ቴክ
በጋዜጣው ሪፖርተር
ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ፣ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ አገልግሎት ይጀምራል ተብሏል።
"አሊ-ኤክስፕረስ" በተሰኘው መተግበርያው የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም የሚሰጥ ኩባንያ መሆኑን ይታወቃል። አሊባባ አገልግሎት ከሚሸጥባቸው አገራት መካከልም ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፤ ግብፅ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡
ኩባንያው ክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋትና ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን ተገልጿል። አሊ ባባ አገልግሎቱ በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት ያለመ መሆኑን በመረጃው ተጠቅሷል።
ኩባንያው የአፍሪካ አገራትን ገንዘቦች በግብይቱ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋሉ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርአት የተነሳ ለአፍሪካዊያን ትልቅ ማነቆ የሆነውን የግብይት ችግር ለመቅረፍ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡
አሊ - ባባ በኢትዮጵያ ያለውን ገበያ ለማስፋፋት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ሲገልፅ የቆየ ሲሆን በዚህም አዳዲስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችን እንደሚያገኝ ተስፋ ማድረጁን ኩባንያው ገልጿል፡፡
ከተለያዩ ኢትዮጵያዊያን የምጣኔ ሐብት አንቀሳቃሾች ጋር ለመስራት ውል ማሰሩንም አይዘነጋም። ከነዚያ መካከል አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከሚመራው ኩባንያ ጋር አብረው ለመስራት ውጥን መያዛቸውን ሁለቱም ተቋማት በጋራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን የሚታወስ ነው።
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ አሊ- ባባ በኢትዮጵያ ገበያ እጅግ ከሚሳቡ የሩቅ ምስራቅ ኩባንያዎች መካከል መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልፅ ቢሰማም፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ገበያ እንቅስቃሴ መች እንደሚጀምር ግን ለረጅም ጊዜ ሲያወዛግብ ቆይቷል።
አሊ ኤክስፕረስ በተሰኘው መተግበርያ በኩል ጥሬ እቃዎች መሸመትና መሸጥና መለወጥ የሚቻልበትን አገልግሎት እንደሚያስጀምር ገልጿል ።
ከየካቲት 17 ጀምሮም በኢትዮጵያ አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ የሚጀምር መሆኑን ኩባንያው ባሰራጨው መረጃ ጠቅሶ ምን የኢትዮ - ቴሌኮም ንብረት ከሆነው ቴሌ ብር ጋር አብረው እንደሚሰሩ ገልጿል።
የአሊ ባባ ባለቤት በአንድ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ግብዣ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ ሲሆን በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ ደረጃ ያለውን ገበያ ማድነቃቸውን የሚታወስ ነው።
በኢትዮጵያም እንዲህ ያለውን መተግበሪያ ከሕዝብ ብዛት አንፃር አስፈላጊ መገበያያ ዘዴ መሆኑንና በሩቅ ምስራቅ ያለውን ልምድ ወደ አገር ቤት እንደሚያስገቡ ጠቅሰው ከመንግሥት ጋር ንግግር እያደረጉ መሆናቸውን አልሸሸጉም።
ለዚህ እንዲረዳው በተጠቀሱት አገራት ከሚገኙ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ጥምረት መፍጠሩን የገለፀው አሊ ባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ማለትም የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ብርን ጨምሮ የተለያዩ ገንዘቦችን በግብይት ስርአቱ ውስጥ እንደሚያካትት አስታውቋል፡፡
አሊባባ ከቴሌ ብር ጋር ለመስራት ቢስማማ ከአሊ ኤክስፕረስ ላይ ኦንላይን [Online] እቃ ለመግዛት ቴሌ ብር ተጠቅሞ መክፈል ይቻላል ማለቱን ባሰራጨው መረጃ አስታውሷል።
ADVERTISEMENTS