ዜና/ ቢዝነስ
ጎዶ ሆምስ ኤክስፖ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ 10,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ይዞታ ቤቶች ለማስገንባት ስራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል ።
በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የሚመለከታቸው አካላትና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በትናንትናው እለት ተከፍቷል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ደረጀ ማሙዮ አክለውም ኤክስፖው በሚኖረው ቆይታ የቤት ፈላጊውን ማህበረሰብ ፍላጎትና አቅም ባገናዘበ መልኩ በቅናሽ በሚቆየው የዋጋ ሁሉም ቤት ፈላጊዎች እንዲሆኑ ውጥን ተይዞ ፕሮጀክቱን መጀመሩን ገልፀዋል።
አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ከተመሰረተ ሶስት ዓመት ገደማ ሲሆን የተለየ ሞዴል ያለው አቀራረብ ይዞ መቅረቡን ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መረዳት ችለናል።
ድርጅቱ ከ150 ድርጅቶች ጋራ እያቋቋመ የሚገኝ ህብረት እንደሆነ ለወደ ፊቱ የቤት አቅርቦት ይፈታሉ ተብለው ከሚጠበቁ የቤት አቅርቦት ሞዴል አንዱ መሆኑን ተገልጿል።
በቅርቡ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የኗሪዎችን የቤት ፍላጎት ለመቅረፍ የግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን በርከት ያሉ ቤቶች እየተገነቡ መሆናቸውን የሚታወቅ ነው።
ከተማ መስተዳድሩ ውጥን መሰረትም የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ ጋር አብሮ ለመስራት እንዲሁም አዲስአበባ ለኗሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ እያደረገው ያለውን እንቅስቃሴ ከዳር እንዲደርስ እገዛ እንደሚፈልግ ሲናገር ይደመጣል።
አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ከ150 ኩባንያዎቹ መካከል አንዱ በሆነው ጎዶ ሃውሲንግ ኤንድ ስማርት ሪል እስቴት ደግሞ የመንግስትና የግል አጋርነት ማለትም 70/30 እሴትን አጣምሮ እየሰራ መሆኑን ከስራ አስፈፃሚው ደረጀ ማሙዮ መረዳት ችለናል።
በአማኑኤል ክንደያ